የቅርብ ጊዜ ይዘቶች
ይዘቶች አልቀዋል
ቅዱሶፊ ምንድን ነው?
ስያሜ
ቅዱሶፊ፡ ቅዱስ እና ሶፊያ(Σοφία) ከሚሉ ሁለት ቃላቶች የተመሰረተ ሲሆን ሶፊያ በግሪክ እውቀት፣ ጥበብ እና ማስተዋል ማለት ነው። ከዚህ በመነሳት ቅዱሶፊ ዶክትሪን የማይገድበውን እውቀት እንዲሁም እውነታን በጥልቀት እና በነፃነት መሻትን ያመለክታል።
ፍልስፍና
ቅድስና እና ጥበብ ከሐይማኖት ባሻገር
ቅዱሶፊ ውስጣዊ እድገትን፣ የሕሊናን መንቃት እና አለማቀፍ እሴቶችን ይደግፋል። ከየትኛውም ሃይማኖት ገለልተኛ ሲሆን፣ ራስን መመልከት፣ ማወቅ እና ከራሳችን ጋር ጥልቅ ግንኙነትን እንድንፈጥር ይረዳናል።
ራዕይ
ቅዱሶፊ፡ መንፈሳዊ አብርሆትን ማስፋፋት ዋነኛ አላማው ነው። በጋራ አዕምሮን በማብራት፣ ነፍሳትን ወደ መገለጥ እና ውስጣዊ ሰላም በመምራት የብርሃን ችቦ ለመሆን እንጥራለን።
የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች